Yearly Archives

2020

ሰበር ዜና ቀሲስ ሳሙኤል ብርሃኑ ሥልጣነ ክህነታቸው ታገደ (ተያዘ)

(አደባባይ ሚዲያ የካቲት 25/2012 ዓ.ም፤ March 4/2020)፡- በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት ሥር በዝርወት ባለችው የደ/ሰ/ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩትና «ኦሮሞ በመሆኔ ተገፋሁ» በሚል ምክንያት አዲስ የኦሮሞ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አቋቁማለኹ በሚል እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙት ቀሲስ ሳሙኤል ብርሃኑ ክህነታቸው መያዙ ታወቀ።

የሞጣ መስጂዶች ጉዳይ እውነቱ ከሐሰቱ ሲለይ፤ ከዚህ በፊት ካልታዩ አነጋጋሪ መረጃዎች ጋር

ስለ ሞጣ መስጂዶች ብዙ ነገር እየተባለ ነው፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ተሰብስቧል። በዚህ ጉዳይ ብዙ ክርስቲያኖችም ተሳታፊ ሆነውበታል። ለመሆኑ በሞጣ ከተቃጠሉት መስጆዶች ጀርባ ምን ሲከናወን ነበር? ምን ያህል ንብረትና ሀብት ተጎዳ? እንደሚባለው የተጎዱት ሙስሊሞች ብቻ ናቸውን? ምን ያህል ክርስቲያኖች ተጎዱ? ዝርዝር መረጃዎችን ይዘናል። እንዳያመልጣችሁ።

OMN ከመንግሥት የተላለፈበትን ቅጣት ገሸሽ ያደረገ መልስ ሰጠ

(አደባባይ ሚድያ የካቲት 25/2012 ዓ.ም፤ March 4/2020) OMN የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ያደረሰውን ማስጠንቀቂያ ባላገናዘበ ሁኔታ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብር እና መብት አስጠባቂ ሕብረት ለቃለ ምልልስ መጋበዙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቱን ትእዛዝ ገሸሽ ያደረገ መሆኑን አንድ የሕግ ባለሙያ ገለጹ። ሚዲያውን በተመለከተ

የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ከምን ደረሰ? «ቤተ ክህነቱም ዝም መጽሐፉም ዝም» ሆነሳ

በቅርቡ የተደረገው የቅ/ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ ብዙ ዐበይት ውሳኔዎችን ማሳለፉ ይታወሳል። ነገር ግን ከዚያ ወዲህ ስለ ውሳኔዎቹ አፈጻጸም ያለው የቤተ ክህነቱ አስፈጻሚነት እንደሚጠበቀው እንዳልሆነ ጉዳዩን የሚከታተሉ ሰዎች በመናገር ላይ ይገኛሉ። ይህንን በተመለከተ የተደረገውን ጥልቅ ውይይት ለመከታተል የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ።

ስለ «ፈይሳ አዱኛ» ታቦት አሰያየም ብፁዕ አቡነ ሚካኤል የሰጡት መልስ

ብፁዕ አቡነ ሚካኤል «የኦሮሚያ ቤተ ክህነት» አስተባባሪዎች ነን ባሉ ሰዎች ሁለት ወሳኝ ስህተቶች ዙሪያ ይህንን የመሰለ አስተማሪ መልስ ያውም ሰዎቹ ባሉበት ሰጥተዋል። ይህንን ንግግር ለመስማት የሚከተለውን የዩቲዩብ ሊንክ ተጫኑ።

ፖለቲካዊ ቋንቋ ከሃይማኖታዊ ቋንቋ ጋር ሲላተም፡- የሲያትል ምእመናን ውዝግብ እንደ ማሳያ

በሲያትል ደብረ ሰላም ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለረዥም ጊዜ ሲያወዛግብ የነበረው እና አሁን የተወሰኑ አባላቱ ጥለው በመውጣታቸው ምክንያት እልባት ያገኘው ልዩነት መዘዙ ምንድርነው? ቋንቋ እና ብሔረሰብ በልዩነቱ ውስጥ እንደምክንያት መጠቀሱ ምን ያህል እውነት ነው?

የ “OMN” ሚዲያ የኢትዮጵይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ይቅርታ እንዲጠይቅ ታዘዘ::

የብሮድካስት ባለስልጣን ማስጠንቀቂያ ለሚዲያው ማስጠንቀቂያ ላከ:: ( አደባባይ ሚዲያ:- የካቲት 18/2012) የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በጃዋር አህመድ ባለቤትነት የሚሰራጨውን "የ ኦ ኤም ኤን" (Omn) ሚዲያን አስጠነቀቀ:: ሚዲያው በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ባስተላለፈው የሀሰት ትርክት እና መሰረተቢስ ፕሮፖጋንዳ