Yearly Archives

2019

«በምትለምን ሀገር የማትለምን ቤተ ክርስቲያን ነች ያለችን» (ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)

(አደባባይ ሚዲያ፣ አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6/2012 ዓ.ም)፡- “ቤተ ክርስቲያን ሆይ፥ ፀሐይሽ አትጠልቅም” በሚል መሪ ቃል ታኅሣሥ 5/2012 ዓ.ም በሚሌኒየም አዳራሽ የተካሔደው እና በአገልጋይ ዕጦት የተዘጉ፣ በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ጥቃትና ተጽዕኖ ሥር ያሉ ሦስት የኦሮሚያ አህጉረ ስብከት አብያተ ክርስቲያንን ለማስከፈትና ለማጠናከር እንዲሁም ገቢ ለማሰባሰብ እና በሆሮጉድሩ…

በኦሮሚያ ቤተ ክርስቲያንን ለማጠናከር ያለመው ጉባዔ በሚሌኒየም አዳራሽ ተካሔደ

(አደባባይ ሚዲያ፣ አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5/2012 ዓ.ም)፡- “ቤተ ክርስቲያን ሆይ፥ ፀሐይሽ አትጠልቅም” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ዛሬ ታኅሣሥ 5/2012 ዓ.ም በሚሌኒየም አዳራሽ ተካሒዷል። በአገልጋይ ዕጦት የተዘጉ፣ በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ጥቃትና ተጽዕኖ ሥር ያሉ ሦስት የኦሮሚያ አህጉረ ስብከት አብያተ ክርስቲያንን ለማስከፈትና ለማጠናከር እንዲሁም…

የጥምቀት ማክበሪያ ቦታ እየነጠቁ «ጥምቀት የእኛም ነው» ማለት ይቻላል?

ውይይት ከጋዜጠኛ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ጋር። በተጨማሪ፡- ስለ ጠ/ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማት እና የሕዝቡ እውነተኛ ስሜት እንዲሁም ከአክሱም 30 ማይልስ ርቆ በቁፋሮ ስለተገኘው የ1700 ዓመት ዕድሜ ቤተ ክርስቲያን ሁናቴ ተወያይተናል።

«ጥምቀት» ዓለማቀፋዊ ቅርስ ሆነ…

(አደባባይ ሚዲያ፤ Dec 12/2019):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በአደባባይ ከምታከብራቸው በዓላት አንዱ የሆነው የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀቱ በዓል ትውፊታዊ አከባበር በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (UNESCO) ጥበቃ ከሚደረግላቸው የማይዳሰሱ የሰው ልጆች ቅርሶች ተርታ መመዝገቡ ታወቀ።…

ኢትዮጵያ ውስጥ “ያለው ግጭት መነሻው መቀለ ነው” (ታዬ ደንደኣ)

(አደባባይ ሚዲያ፣ ሕዳር 29/2012 ዓ.ም፤ Dec. 9/2019):- የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ ታዬ ደንደኣ ኢትዮጵያ ውስጥ "ያለው ግጭት መነሻው መቀለ ነው" ሲሉ ተናገሩ። በኦሮምኛ ቋንቋ በጻፉትና በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት አነጋጋሪ ጽሑፍ ችግሩ የሚመነጨው ከመቀለ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ታዬ "ሀገራዊ ረብሻ ለማስነሳት ወያኔ 400 ሚሊዮን ብር…

በምሥራቅ ወለጋ በአማራ ብሔረሰብ አባላት ላይ አደጋ እንዳንዣበበ እየተገለፀ ነው

(አደባባይ ሚዲያ):- OMN ዛሬ ሕዳር 28/2012 ዓ.ም በኦሮምኛ ባቀረበው ዜና "በ1998 ዓ.ም ከአማራ ክልል መጥተው በምሥራቅ ወለጋ ጉደያ ወረዳ የሠፈሩ የአማራ ተወላጆች ስጋት ሆነውብናል ሲሉ የአካባቢው የኦሮሞ ማኅበረሰብ አቤቱታ አቀረቡ" ሲል የሠራው ዘገባ በአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ላይ አደጋ እያንዣበበ መሆኑን ይጠቁማል ሲሉ የአደባባይ ሚዲያ ባለሙያዎች ገለፁ::…

ጣሊያን ሰልፍ አስተናግዳለች

(አደባባይ ሚዲያ):- በ26/03/12ዓም በትላንትናው ዕለት በጣልያንና በአካባቢው ሀገረ ስብከት የተከናወነው የሮማው መንፈሳዊ ሰልፍ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በሰላም ተጠናቋል። ሰልፉ የተጠራው በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ በአውሮፓ የሚገኙ ሀገረ ስብከቶች በአንድ ላይ በመሆን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት በተያዘለት ቀጠሮ መሠረት ነው። ሰልፉ ከጠዋቱ በአራት ሰዓት በሮም ፖርላሜንቶ ጽሕፈት…