Yearly Archives

2020

ሰበር ዜና (ዘአደባባይ) ——በፖሊስ የታሰሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው የተባሉት ንቡረዕድ አባ ዮሐንስ…

በቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 24 የተሠራውን መቃኞ ሌሊት ለማፍረስ በተላከውሕገ ወጥ ፖሊስ ሽብር የሁለት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ ፖሊስ አንድ አባት ማሠሩ ተሰምቷል። በፖሊስ የታሰሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው የተባሉት ንቡረዕድ አባ ዮሐንስ ናቸው። ለምን እና እንዴት እንደታሰሩ፣ የሥራ ኃላፊነታቸው ምን እንደሆነ በማጣራት ላይ

የጎጤ ቤተ ክህነት ተቃርኖ (በዮሐንስ መኮንን)

የዘውግ ቤተ ክህነትና በቋንቋ መገልገል ሁለት የሚቃረኑ ነገሮች ናቸው፡፡ የጎሳ ቤተ ክህነት የፖለቲካ ጥያቄ ሲሆን በቋንቋ መገልገል ግን የድኅነት ጥያቄ ነው፡፡ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ፣ በወላይትኛ፣ በሶማልኛ፣ በአፋርኛ ወዘተ... የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማግኘት የአማኙ ክርስቲያናዊ መብት፣ የቤተ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ደግሞ ግዴታ ነው፡፡ እንደ ክርስትና ይህ

«በሀገረ ስብከቴ ምንም ዓይነት ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ እንዳይኖር በጥንቃቄ እየሠራሁ ነው» (ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ)

(አደባባይ ሚዲያ፤ ጥር 29/2012 ዓ.ም፤ Feb. 7/2020)፡- ራሱን «የኦሮሚያ ቤተ-ክህነት አደራጅ ኮሚቴ» ብሎ የሚጠራው ቡድን ሰሞኑን በሚኒሶታ ሊያደርገው አቅዶታል ለተባለው እንቅስቃሴ «ምንም ዓይነት እውቅና አልተሰጠውም» ሲሉ የሜኔሶታ እና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ለአደባባይ ሚዲያ ገለፁ። ከሀገር ቤት ጽላት ያሉትን

ፖሊስ ሌሊቱን ቤተ ክርስቲያን ለማፍረስ ባደረገው ጥረት ሁለት ሰዎች ተገደሉ፣ የጅምላ አፈሳ ተካሒዷል

(አደባባይ ሚዲያ፣ ጥር 26/2012 ዓ.ም፤ Feb. 4/2020)፡- አዲስ አበባ 22 መንገድ፣ ቅዱስ ገብርኤልን ሆስፒታል አካባቢ አፍሮ ጽዮን ኮንስትራክሽን ጎን ካለው ክፍት ቦታ ላይ ለብዙ ዓመታት ክፍት የነበረ ቦታ የተሠራ ቤተ ክርስቲያንን በሌሊት ለማፍረስ በተደረገ ጥረት ሁለት ክርስቲያኖች ተገደሉ። ስለ ጉዳዩ እማኝነታቸውን ያቀረቡት ጋዜጠኞቹ ሀብታሙ ምናለ እና

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ እየገባ መሆኑ ተነቀፈ

(አደባባይ ሚዲያ፣ ጥር 26/2012 ዓ.ም፤ Feb. 3/2020) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት መቀጠሉ አማኞቿን በማስቆጣት ላይ እንደሚገኝ አንድ ከፍተኛ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ኃላፊ አስታወቁ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ