የ“ራእየ ማርያም” ትርጉም ችግር

(አምሳሉ ተፈራ – ከሙኒክ/ጀርመን)
በተለይ ለአደባባይ www.adebabay.com የጡመራ መድረክ የተዘጋጀ
ሀ. ጠቅለል ያለ መነሻ
በቅድሚያ ሰሞኑን በተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች የውይይት ርእስ ሆኖ እየተነሣ ያለውን “ራእየ ማርያም” መጽሐፍ አስመልክቶ አንዳንድ ነጥቦችን እንዳጋራ ወንድሜ ኤፍሬም እሸቴ ስለጋበዘኝ ከልብ ማመሥገን እፈልጋለሁ። እሱ በሚያካሂደው “አደባባይ” የጡመራ መድረክ የተካሄደውን ውይይት (እርሱ ከመምህር ፍሥሓ ታደሰ ጋር ያደረገውን) አዳመጥኩት። ውይይቱ አስተማሪ ሲሆን በጣም በሳል ሃሣቦችም ተዳሰዋል። እንደዚሁም በኢትዮጵያ ጥናት መስክ ግንባር ቀደም ተጠቃሽና ዓለም አቀፍ ምሁር የሆኑት ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ “Vision of Mary (ራእየ፡ ማርያም፡) Under Attack” በሚል ርዕስ የጻፉት በእጅጉ አስተማሪ ነው። ይኽንን የፕ/ር ጌታቸው ጽሑፍ በተሰጠው ርእስ በጉግል ላይ የተለያዩ ገጸ-ድሮች ተጋርተውት ስላለ በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። እኔም ከዚህ በላይ ልጨምረው የምችለው ብዙም ባይኖረኝም ከራእየ ማርያም ውስጥ የነገድና ብሔር ስም የሚያነሳውን ገጽ ትርጉም እና ስለ መጽሐፉ ጠቅለል ያለ ግንዛቤ እንዲኖረን አንዳንድ ነጥቦችን ለማንሳት እፈልጋለሁ።

ተጨማሪ

Comments are closed.