ሌላ ገመዶ ዳሌን አለ እንዴ?

ዶ/ር ገመዶ ዳሌን በቅርበት አውቀዋለሁ አርሲ ውስጥ ከእስላም ቤተሰብ ተወልዶ ያደገ 39 እህትና ወንድም ያለው በወጣትነት ዘመኑ ከእስልምና ኮብልሎ አድቬንቲስት የተሰኘውን የፕሮቴስታንት ዘውግ የተቀላቀለ ሰው ነው።

በሙያ ስም በርካታ ነውሮችን ሲያደርግ የነበረ ነውረኛም ነው። በተለይም የኢትዮጵያ ብዝኀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በነበረበት ወቅት “shashemenie botanical garden” ማቋቋም በሚል ሰበብ የሕዝብና የመንግሥት ገንዘብ ዘግኖ አርሲነገሌ ላይ በግሉ አንድ የአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ማሰራቱ የአደባባይ ምስጢር ነው። እነ ሎሬት ዶ/ር መላኩ ወረደ (የልጅ Tedla Melaku አባት) የሀገርን ብዝኀ ሕይወት ይጠብቅ ዘንድ ቀን ከሌሊት ደክመው የሰሩትን ተቋም የፕሮቴስታንት ቸርች አስመስሎ እንዳይራመድ ቀይዶ የሰራው ማን ሆነና ነው?

እናም ይህ ሰው በዛሬው የፓርላማ ውሎ ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት በቀረበው የቦርድ ሹመት ላይ ሌላውን ሃይማኖት ይጠላል የሃይማኖት ብዝኀነትን አያከብርም እያለ ሲናገር ባየው ገረመኝ። ሌላ ገመዶ ዳሌ አለ እንዴ ስልም ራሴን የሞኝ ጥያቄ ጠየቅሁት። ስመጥሩን ተቋም እግር ተወርች በዘርና በሃይማኖት ቅያድ አስሮ ሽባ ያደረገ ፓስተር በዚህ ደረጃ አፉን ሞልቶ ሲናገር ሳይ ስራችን ገና እንዳልተጀመረ ገባኝ።

ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመረረ ጥላቻ ያለው ይህ ሰው አይደለም የአንድ ዳይሬክቶሬት ሃላፊን ይቅርና አዲስ ተቀጣሪን እንኳ አድቬንቲስት ካልሆነ የማያስተናግድ ሰው ነበር።

ተቋሙን ለቆቆ እንኳን ዛሬም ድረስ ጠባሳው እንዳልለቀቀ አሁንም ጎራ ብሎ ማየት ይቻላል። የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚንስትር ሆኖ ተሹሞ
ከባዮ ዳይቨርሲቲ (ብዝኀ ሕይወት) ኢንስቲትዩት ከለቀቀ በኋላም ይህንን ሚኒስቴር ሳይንሳዊ ሳይሆን እንዴት ፕሮቴስታንታዊ አድርጎ አፍርሶ እንደሰራው ብዙዎቻችን የምናውቀው ሃቅ ነው።
እናም ይኸ በመንግሥት ገንዘብ ቸርች የሚገነባ ሰው የዳንኤልን ሹመት ተቃወመ ነው የምትሉኝ?
ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቆረንጮ አንጥፉልኝ አለ ማለት ይሄኔ ነው።

ሰውየውስ ጥሩ የፍትህ ስርዓት የለንም እንጅ ቢኖረን ላደረሰው ሁሉ ሃገራዊ በደል ዘብጥያ የሚወርድ እንጅ ቤተመንግሥት ገብቶ በመጻኢ እድላችን ላይ ገብቶ እንዲፈተፍት የሚፈቀድለት አልነበረም።
ምን ታረገዋለህ።

Comments are closed.