መትፋት ያስነውራል!!!

(Birhanu tekleyared እንደጻፈው)

ጊዜ መልካም ነው “ስሙን ለሰው አወረሰው” የሚለው የሀገራችን ብሂል ዛሬ ግዘፍ ነስቶ ፓርላማው ላይ ሲንጎማለል አሳየን የፓርላማ አባላቱም በራሳቸው ስም ዲያቆን ዳንኤልን ሲጠሩት ዋሉ።

እንለፈው ተብሎ እንጂ………………

በምርጫ 2007 ኮሮጆ ገልብጦ፣ተቃዋሚዎችን አስሮና ገድሎ፣መራጮችን አሸማቅቆ በደም ላይ የተመሰረተ ፓርላማ እንደሆነ አጥተነው አይደለም።

እንለፈው ተብሎ እንጂ………………………

በሀይማኖት እኩልነት የማያምነው ዲያቆን ዳንኤል ሳይሆን ዛሬ ተቃውሞ ያነሳው መንጋ የፓርላማ አባል ነው። ማነው በየተመረጠበት ወረዳ የቤተ እምነት ይዞታዎችን እየሸነሸነ ለግል ጥቅሙ እያዋለ የእምነት ተቋማትን የሚያበላልጠው? ከአብያተ ክርስቲያናትና መስኪዶች መቃጠል ጀርባ ያለው ማነው?

ደግሞም…….
በዜጎች መካከል ክፍፍል እንዲፈጠር የሚሰሩት ዲያቆን ዳንኤል ወይስ ፅሙማኑ የፓርላማ አባላት? ማነው ከፋፋይ ታሪክ በሙሉ ድምፅ ያፀደቀው? የህወሓት የጡት ልጅ የኦህዴድ ሚስት የኦነግ ውሽማ ሆነው በአክቲቪስቶች እየተመሩ እጅ የሚያወጡና የሚያወርዱ መሆናቸውን ህዝቡ የማያውቅ መስሏቸው ይሆን?

የዲያቆን ዳንኤል ሀጢአት እንደሌሎቹ ለሹመት ሲል ሀይማኖት አልባ ነኝ አለማለቱና ቤተክርስቲያንን ማገልገሉ ነው። የዲያቆን ዳንኤል ጥፋት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰባኪና ቤተክርስቲያኔን አላስነካም የሌሎችም እምነት መብት በተገቢው መልኩ ይከበሩ ማለቱ ነው። የዲያቆን ዳንኤል ጥፋት ቤተክርስቲያን የሰጠችውን የክህነት ስልጣን አክብሮ በየአደባባዩ በልበ ሙሉነት “ዲያቆን” ተብሎ መጠራቱ ነው።

በረከታቸው ይደርብንና አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እንዲህ አይነት ነገርን የምናልፍበት ልዩ ኪኒን አዘውልናል። መድሀኒቷ “ስራህን ስራ” ትሰኛለች። የዛሬውን የጉባዔ ሰረቅት ጫጫታን ወደጎን ብለን ስራችንን እንስራ። ኦርቶዶክስ ጠሎች ሳያውቁት እያነቁን ነውና በዚህ ንቃታችን እንቀጥል። መጪው የምርጫ ጊዜ ነውና ሚናችን ምንድነው? ምን እንስራ? ምንስ ይጠበቅብናል? በሚሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት እናድርግ። ለምርጫው እንዘጋጅ ያኔ ከቀሳጢዎች ሁሉ ጋር መሬቱ ላይ እንገናኛለን

ደግነቱ ዲያቆን ዳንኤል የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ተማሪ ነው እኛም የመንፈስ ልጆቻቸው ነንና

“ስራችንን እንስራ”

ይኸው ነው!!!

Comments are closed.