OMN ከመንግሥት የተላለፈበትን ቅጣት ገሸሽ ያደረገ መልስ ሰጠ

(አደባባይ ሚድያ የካቲት 25/2012 ዓ.ም፤ March 4/2020)
OMN የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ያደረሰውን ማስጠንቀቂያ ባላገናዘበ ሁኔታ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብር እና መብት አስጠባቂ ሕብረት ለቃለ ምልልስ መጋበዙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቱን ትእዛዝ ገሸሽ ያደረገ መሆኑን አንድ የሕግ ባለሙያ ገለጹ።

ሚዲያውን በተመለከተ ያለውን የእስካሁን የደብዳቤ ምልልስ በአጭሩ ያስረዱት የሕግ ባለሙያው «ጴጥሮሳውያን በዘገባው ላይ ቅሬታቸውን ለባለስልጣን መ/ቤቱ አቀረቡ። ባለስልጣን መ/ቤቱ በ03/06/12 omn በቅሬታው ላይ መልስ እንዲሰጥ ጠየቀው። ምንም አላጠፋሁም የሚል ድፍን ያለ መልስ ሰጠ። ድርጊቱ በአዋጅ ቁጥር 533/1999 መሠረት ጥፋት ሆኖ ስለተገኘ በ18/06/12 ሚዲያው ለጥፋቱ ቤተ ክርስቲያንን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ የማስተባበያ ፕሮግራም ሠርቶ እንዲያስተላልፍ ታዘዘ፤ OMN የመጨረሻዋ ቅጣት ስትደርሰው ያልሰማ በመምሰል በ19/06/12 ጴጥሮሳውያንን ለቃለ መጠይቅ ጠራ።…. የOMN ሐሳብ ቃለ መጠይቅ አድርጊያለሁ በማለት ማጣራት ተደርጎ ጥፋተኝነቱ አለመረጋገጡን ለማሳየት፣ ቤተ ክርስቲያንንም ይቅርታ ላለመጠየቅ፣ በአጠቃላይ ጉዩን አድበስብሶ ለማለፍ የተደረገ ሙከራ ነው» ሲሉ የሕግ ባለሙያው ነገሩን በዝርዝር አስረድተዋል።

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ OMN እያሳየ ያለውን ከሕግ በላይ የመሆን አዝማሚያ እንዴት እንደሚመለከተው ወደፊት የሚታይ ይሆናል።

Comments are closed.