የእስላም አክራሪ ጠብ አጫሪነት ከቀን ወደ ቀን እየገፋ ነው

Ze Addis (ከሀገረ አሜሪካ)

የእስላም አክራሪ ጠብ አጫሪነት ከቀን ወደ ቀን እየገፋ ነው
***********
አደባባይ ቴሌቪንን ወደ ሳተላይት ለምን አናሳድገውም*

ሀገራችን ላይ ከሚታተሙት እስልምና ተኮር መጽሔቶች አንዱ ቀሰም ነው፡፡ ይህ መጽሔት እስልምና ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ በዚህ መጽሔት ላይ የሚወጡ ጽሁፎች፣ ሁል ግዜ ሊባል በሚችል መልኩ በተዛዋሪ ወይም በግልጽ ክርስትና ላይ ጅራፍ የሚያጮሁ ናቸው፡፡ ስለ እስልምና ከሚያትተው በላይ ፣ በርካታ ጽሁፎቹ ክርስትናን ማጥላላት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው፡፡ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ላይ የሚያጠነጥኑ ትንኮሳዊ ጽሁፎችና ምስሎች ለዚህ መጽሄት የተለመዱ ናቸው፡፡ የክርስትና በተለይም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆነውን ሁሉ ጥላሼት በመቀባትና ስለ ሃይማኖቷ ፊት ቆመው የሚታዩትን ወገኖች ማሳደድ በርክቷል፡፡

በቅርቡ የወጣው የቀሰም መጽሄትን እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል፡፡ የዚህ መጽሄት ሽፋን ላይ “እስላም ነህ አማራ” በሚል ርዕስ የተለጠፈውን ጽሁፍና ምስል ማየት በቂ ነው፡፡ ዛፉ ስሮቹ አጼ ዮሓንስ፣ አጼ ምኒልክና አጼ ኃይለሥላሴ ሲሆኑ፣ ፍሬዎቹ ላይ ከሚታዪት ስምንት ሰዎች ውስጥ አምስቱ የቤተ ክርስትያን ሰዎች ( መልአከ ኤዶም ኤፍሬም ፣ ዲያቆን ዳንኤል፣ መምሕር ምሕረተ አብ፣ መምሕር ዘመድኩንና የቴዎሎጂ ምሩቅ የሆኑት ዲያቆን ሃብታሙ) ናቸው፡፡

የምስሉ መልዕክትም ብዙ ነው ፡፡ መንፈሳዊም ፖለቲካዊም አንድምታ አለው፡፡በፖለቲካው አማራ ብሎ እስላም ስለሌለ እስላሞች አማራ አይደላችሁም የሚል ነው፡፡ሌላው ደግሞ እነዚህን ስማቸው የተጠቀሱትን የቤተ ክርስትያን ሰዎች በጸረ እስላምነት ፈርጆ ስም ማጥፋት ( character assassination)ና በማሸማቀቅና በጉ ስራቸውን እንዲያቆሙ ስነ አዕምሯዊ የሚድያ ጦርነት መክፈት ነው፡፡ ባጭሩ ሽፋን መጽሄት ላይ የተሳለው ፓስተር 9 ምስል ) መልክት ፣ ከላይ የተጠቀሱት መምህራን ጸረ እስላም እንደሆኑና የሚሰሩትም ለአንድ ብሄርና ሃይማኖት ስለሆነ ሌሎቻችሁ አትቀበሏቸው ነው፡፡
ለምን ተዘመተባቸው?

መልአከ ኤዶም ኤፍሬም በቅርቡ አደባባይ የተሰኘውን ሚድያ በማስፋት (ከጡመራ ወደ ተነቀሳቃሽ ምስል) ፣ ሕዝበ ክርስትያኑን በከፍተኛ ሁኔታ እየደረሱት ነው፡፡ ሚድያው በተጀመረ በጥቂት ግዜያት ውስጥ እጅግ የብዙ ዜጎችንን አመኔታና እይታ ማግኘት ችሏል፡፡ ወደፊትም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ከፍተኛ ተጽኖ ፈጣሪ ሚድያዎች መካከል እንደሚሆን ጅምሩና ውጤቱ ምስክር ነው፡፡ይህን ሚድያ መግደልና ማስቆም የሚቻለው መስራቹን በማጥላላትና ስም በማጥፋት ነው ብለው ያሰሉ ሰዎች መል አከ ኤዶም ላይ ስም ማጥፋት ዘመቻ በዚህ መልኩ ቀጥለዋል፡፡ ባለቤቱን ሲንቁ፣ አጥሩን ይነቀንቁ

መመሕር ዘመድኩን ክርስትና ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት ተቀን የሚጽፉና አልፎ ተርፎም ለተጎዱ ቤተ አምነቶች በርካታ ድጋፍ የሚያሰባስቡ የቤተ ክርስትያኒቱ መምህርና የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው፡፡ በጽሁፋቸው የሚደሰቱም የሚከፉም ቢኖሩም፣ አንድ ሀቅ ግን አለ፡፡ መምህር ዘመድኩን በዚህ ጨለማ ዘመን ቤተ ክርስትያንና ክርስትያን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በማሳወቅና ክርስትያኑን በማስገንዘብ ደረጃ የተጫወቱት ሚና ቀላል አይደለም፡፡ ታሪክም አይረሳውም፡፡ መምህር ዘመድኩንን ላይም የተጀመረው ዘመቻ ግልጽ ነው፡፡ የስነ ልቦና እና የ ሚድያ ጦርነት ተከፍቶባቸዋል፡፡ ባለቤቱን ሲንቁ ፣ አጥሩን ይነቀንቁ
መምሕር ምሕረተ አብም ሌላኛው የቤተ ክርስትያን መምህር ናቸው፡፡ በተለይም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ፣ ቤተ ክርስትያን ላይ የሚደርሰውን ጥቃትና ክርትያኖች ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ባደባባይ በማውገዝ ጎልተው እየወቱና ብዙ ሕዝብም እየሰማቸው ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ያስደንደገጣቸው እኩያን መምሕር ምህረተ አብም ላይ ዘመቻውን አጧጡፈውታል፡፡ ባለቤቱን ሲንቁ ፣ አጥሩን ይነቀንቁ
ዲያቆን ሃብታሙም የቅድስት ሥላሴ ቴዎሎጂ ምሩቅ የቤተ ክርስትያን ምሁር ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በፖለቲካው ላይ ጉልህ ተሳትፎ ቢኖራቸውም፣ ክርስትናና ላይ የሚደረግ ግፍን አምርረው ከሚቃወሙ ወገኖች አንደኛው በመሆናቸው እሳቸውም የስም ማጥፋቱና የሚድያ ዘመቻው ሰለባ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የትውልድ መምህር ናቸው፡፡ በዚህ ዘመን መስማትና ማንበብ የሚችል ሰው ፣ በአንድም በሌላም የዲያቆኑን ትምህርት ወይም ምክር ያልሰማ አለ ብዬ አላምንም፡፡ ሀገሪቷ ውስጥ ካሉ ትልቅ ተጽኖ ፈጣሪ ሰዎች መሀልም አንዱና ከዋናዎቹ ተርታ ውስጥ ያሉ ሰው ናቸው፡፡ በቤተ ክርስትያኒቱ ላይ የሚፈጠሩ ጥያቄዎች ፣ ጉዳቶች እና መሰል ጉዳዮች የመጀመርያው መልስ ባብዛኛ ው ከዲያቆን ዳ ን ኤል ክብረት ነው፡፡ አልፈው ተርፈው ፣ አሁን የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ናቸው፡፡ እሳቸውም ላይ የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ ምክኛቱ ግልጽ ነው፡፡

መፍትሄው ምንድነው?
“ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ” ይላሉ አበው፡፡ በክርስትናውና በክርስትያኖች ዘንድ ያለው እንቅልፍ መብዛቱን ያዩት አክራሪዎች በቀጥታ ክርስትናን እየተነኮሱ ነው፡፡ ንቀቱም ስለበዛ ፣ የክርስትናን አጥር እየነቀነቁት ነው፡፡ከዚህ በላይ ነገር ፍለጋ ምን አለ? ስለ ራስ ሃይማኖት ማስተማር አንድ ነገር ነው፡፡ ነገር ግ ን የሌላ ሃይማኖትን መምህራን ስብዕናን እያጠፉ ምስልና ፕሮፕፓጋንዳ ማሰራጨት አላማው ግልጽ ነው፡፡
መፍትሄው አንድ ነው፡፡ የሚወረወርብንን ድንጋይ መወጣጫ በማድረግ ትንኮሳን መመከት ነው፡፡ ስለዚህም
1. ከጅምሩ እንዲህ ጠላትን ያስደነገጠውን አደባባይን እስከ ሳተላይት ቲቪ ድረስ ማሳደግ
2. የነ መምህር ዘመድኩንን ፔጅ በብዛት መቀላቀልና በሰፊው ሼር ማድረግ
3. እንደ መምህር ምሕረተ አብ ያሉትን መምህራን ብዙ ቦታ እንዲደርሱ ሃላፊነታችንን መወጣት
4. ሌላውን ብንተወው ፣ ዲያቆብ ዳንኤል ለኛ የሃይማኖት መምህራችን ነው፡፡ የሚያሳዝነው ሰው ማጥፋት እንጂ ሰው ማውጣት አልቻልንም፡፡ አንድ እሱ ቢታይ እሱን ለማድቀቅ ድንጋይ የምንወረውረው እኛው ነን፡፡ በፖለቲካው ባንስማማ እንኳን በሃይማኖት አንድ ነን፡፡ ሁሌም ይሄንን እናስብ እስቲ ጨምሩበት ፤ እንወያይ

Comments are closed.