3 ጳጳሳት የተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ ተቃወመ፣ መግለጫ ሰጠ

(አደባባይ ሚዲያ የካቲት 13/2012 ዓ.ም፤ Feb.21/2020):- በኦፌኮ ፓርቲ መሪነት በኦፌኮ ፓርቲ ቢሮ በተደረገ ስብሰባ የተገኙ ጳጳሳት “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት” የተባለው ቡድን ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ተቃወሙ፤ መግለጫም ሰጡ።

አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ሚካኤልና አቡነ ዜና ማርቆስ በተገኙበት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ መቃወማቸውንና በራሳቸው ርምጃ ለመውሰድ መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

ይህ “አቡነ ሳዊሮስን በበላይነት (እጩ ፓትርያርክ)” አድርጎ የሚንቀሳቀሰው ስብስብ ቅ/ሲኖዶስ የያዘውን ክህነት እንደማይቀበሉና ከተወሰነ አካባቢ የመጡ ጳጳሳት ያደረጉት ውሳኔ ነው ብሎታል ውሳኔውን።

Comments are closed.