Yearly Archives

2020

ኤርምያስ አመልጋና ሌሎች 62 ሰዎች ተፈቱ

(አደባባይ ሚዲያ [የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም፤ Feb. 25/2020):- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክሳቸዉ እንዲቋረጥና እንዲፈቱ የተደረጉ ግለሰቦችን ስም ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ ታዋቂው የቢዝነስ ሰው ኤርምያስ አመልጋ ከተለቀቁት አንዱ መሆናቸው ታውቋል። አቶ ኤርምያስ በኢትዮጵያ ንግድ ማሕበረሰብ ዘንድ በአዳዲስ የቢዝነስ ሐሳብ ፈጠራዎቻቸው የሚታወቁ ሰው ናቸው።

«ቅዱስ ሲኖዶስ በድምጽ ብልጫ አይወስንም።»

ራሱን «የኦሮሚያ ቤተ ክህነት» ብሎ የሚጠራው ቡድን መሪዎች ክህነታቸው ከተያዘ በኋላ ይህንን የቅ/ውሳኔ የተቃወሙ ሦስት ብፁዓን አባቶች መግለጫ መስጠታቸው ይታወቃል። በመግለጫቸውም ላይ ቅለ ቅ/ሲኖዶሱ አሠራር ያነሷቸው ሐሳቦች ነበሩ። ይህንን በተመለከተ ከዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል። ይህንን ወሳኝ ውይይት እንድትከታተሉ

«ከቱርክ የሚላክ አስተምህሮ እና ሽጉጥ የኢትዮጵያ አደጋ እየሆነ ነው»

አደባባይ ሚዲያ ከኢትዮ 360 ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኙ ሀብታሙ አያሌው ጋር በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳዮች ዙሪያ፥ ስለ መጪው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ እና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ አጭር ቶይታ አድርገናል ተከታተሉት። መልካም ምልከታ አስታውሱ ሰብስክራብ እና ሼር ማድረግ እንዳትረሱ፤

3 ጳጳሳት የተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ ተቃወመ፣ መግለጫ ሰጠ

(አደባባይ ሚዲያ የካቲት 13/2012 ዓ.ም፤ Feb.21/2020):- በኦፌኮ ፓርቲ መሪነት በኦፌኮ ፓርቲ ቢሮ በተደረገ ስብሰባ የተገኙ ጳጳሳት "የኦሮሚያ ቤተ ክህነት" የተባለው ቡድን ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ተቃወሙ፤ መግለጫም ሰጡ። አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ሚካኤልና አቡነ ዜና ማርቆስ በተገኙበት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ መቃወማቸውንና በራሳቸው

የእስላም አክራሪ ጠብ አጫሪነት ከቀን ወደ ቀን እየገፋ ነው

Ze Addis (ከሀገረ አሜሪካ) የእስላም አክራሪ ጠብ አጫሪነት ከቀን ወደ ቀን እየገፋ ነው *********** አደባባይ ቴሌቪንን ወደ ሳተላይት ለምን አናሳድገውም* ሀገራችን ላይ ከሚታተሙት እስልምና ተኮር መጽሔቶች አንዱ ቀሰም ነው፡፡ ይህ መጽሔት እስልምና ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ በዚህ መጽሔት ላይ የሚወጡ ጽሁፎች፣ ሁል ግዜ ሊባል በሚችል መልኩ

ቅዱስ ሲኖዶስ: ቤተ ክርስቲያንን በማጠልሸት በተጠመዱ የብዙኀን መገናኛዎች እና ፓርቲዎች ጉዳይ እየተወያየ ነው ————-

(ሐራ ዘተዋሕዶ ዛሬ እንደዘገበው) • በእነቀሲስ በላይ መኰንን ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ አፈጻጸም ገመገመ፤ • “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት” በሚል ሕገ ወጥ እንቅስቃሴው፣ በሕግ እንዲጠየቅ ቢወስንም፣ አፈጻጸሙን በዕርቅ ስም ያሰናከሉ አባቶችንና አካላትን በድክመት ገሠጸ፤ • ሕገ ወጥ እንቅስቃሴውን ከሚደግፉ አባቶች ውስጥ፣ “ብፁዕ ወቅዱስ” እየተባሉ በጸሎት መጠራት የጀመሩ እንዳሉ