የጎሳ ፖለቲካ መጨረሻው ሒትለራዊ ጭፍጨፋ ነው።

OMN ዛሬ በቀጥታ ሕጻን ሽማግሌ፣ ገጠር ከተማ ሳይል በቀጥታ ባስተላለፈው እና አደባባይ ሚዲያ በተረጎመው ንግግር ላይ «ሐበሻ ያገባችሁ በሙሉ ትዳራችሁን» ፍቱ መባሉን OMN እንደ ቀልድ እንድንመለከተው ሊነግረን ሞክሯል። ቀልድ እንዳልሆነ፣ ቀልድም ቢሆን «ሳይጣናዊ ቀልድ» መሆኑን እኛም አይጠፋንም እነሱም አይጠፋቸውም። ጥያቄው ይህ የልጅቱ ንግግር የዚህች ልጅ ብቻ ነው ወይንስ በጎሰኞች መንደር (አማራ በለው ትግሬ ወይም ኦሮሞ) የተለመደ «የደም ጥራት» ችግር ነው?

የልጅቱ ንግግር የሷ ብቻ አይደለም። በቀለ ገርባ ባደረገው «ቋንቋችሁን ካላወቁ ከነርሱ ጋር አትገበያዩ» ንግግር ውስጥ አለ። እሱ በምሁራዊ ቃና ከሽኖ ያቀረባትን ልጅቱ በወጣትነት የብስለት ማጣት ደረቅ አጥንቱን ግጥጥ አድርጋ ተናገረችው።

እስኪ በአካባቢያችሁ ተመልከቱ፡- በጎሰኛ ፖለቲካ ምክንያት ትዳራቸውን የበተኑ ሰዎች አይታችም አታውቁም? እዚህ አሜሪካ ሀገር በዚሁ የጎሳ ፖለቲካ ጡዘት ምክንያት የተበታተኑ ትዳሮችን አይተናል። ከዚህ አንጻር ጎሰኝነትን ከሥር መሠረቱ ነቅለን ለመጣል መዘጋጀት እንጂ በመቀባባት መፍትሔ ማምጣት እንደማንችል ማወቅ አለብን። ዛሬ ትዳራችሁን ፍቱ ያሉ ሰዎች ነገ መሣሪያ ሲጨብጡ ወደ ሒትለሪ ጭፍጨፋ እንደሚሄዱ ከሩዋንዳ ተምረናል።

Comments are closed.