Membership form

የአደባባይ ቤተሰብ ይሁኑ

«የሁላችንም ስለሆነች ኢትዮጵያ በአደባባይ እንዘግባለን።»

Overview አጠቃሎ

አደባባይ ሚዲያ በወገንተኝነት፣ በጊዜአዊ ጥቅም እና አጋርነት ብቻ የሚደረግ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ጋዜጠኝነት ጥቅም እንደሌለው በመረዳት ዕውቀትና መረጃ ላይ የተመረኮዘ፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ፣ ሀገርንና ወገንን በመጥቀም ላይ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍ ባለ ብዙ ቋንቋዎች ሚዲያ እንዲሆን ታልሞ የተጀመረ ነው።

Vision ርእይ

ዘመኑን የዋጀ ሥልጣኔን መሠረት ያደረገ የነጠረ እውነታ ለኢትዮጵያውያን ደግሞም ለሉላዊው ማኅበረሰብ በቀላሉ ማድረስ፤

Mission ተልእኮ

አደባባይ ሚዲያ በኢትዮጵያ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሃይማኖታዊ እንዲሁም ባህላዊ ጉዳዮች ላይ ሙያዊ ዜናዎች፣ ሐተታዎች፣ ዘገባዎች እና ዶኩመንተሪዎችን (ጥናታዊ ዘገባዎች) ለእውነት በመወገን በላቀ ጥራት እና በብቁ ባለሙያዎች በመታገዘ እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ መረጃ ለኢትዮጵያውያን ደግሞም ለሉላዊው (global) ማኅበረሰብ ከትርፍ ነፃ በኾነ አደረጃጀት ማቅረብ፤

Goals ግቦች

  • አገራችንና ሕዝቦቿን የሚጠቅም ሁሉን አቀፍ፣ ሚዛናዊ መረጃና «የነጠረ እውነታ» ማቅረብ፣
  • በአገራችን ስለሚደረገው ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳይ ለማንም ያልወገነ መረጃ በተለያየ መንገድ ማቅረብ፣
  • ቴክኖሎጂው በሚጠይቀው የመረጃ ማሠራጫ መንገድ በቴሌቪዥን፣ በእጅ ስልኮች፣ በታብሌቶች እና በኮምፒውተሮች እና በሌሎች  በቀላሉ ተደራሽ ሊሆኑ በሚችሉ መንገዶች ሁሉ መረጃን ለአድማጭ ተመልካች ማድረስ፣
  • የተሻለ ተደራሽነት ባለው መንገድ (ለምሳሌ በሳተላይት) በቴሌቪዥን የሚቀርቡ ዝግጅቶችን ማቅረብ፣

ትኩረት

  • ሚዲያችን ራሱን የቻለና በሁለት እግሩ የቆመ ሚዲያ እንዲሆን በትርፍ አልባ ድርጅትነት ማቋቋሙ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን።
  • በዘመናችን ያለውን የሚዲያዎች ዕድገት የሚከታተሉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጥንታዊ ሚዲያዎች (traditional media) የሚባሉት ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ሬዲዮና ቴሌሺዥን ዘመን ባመጣው የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ እየተበለጡ በመምጣታቸው አንባቢ አድማጭና ተመልካቻቸው እየቀነሰ በመምጣት ላይ ይገኛል። በአገራችንም የሚኖረው መጻዒ ዕድል ከዚያ ውጪ አይሆንም።
  • ከዚህ አንጻር ዋነኛ ሚዲያችንን ትርፍ አልባ (nonprofit media) እና ኢንተርኔት መር ሚዲያ ማድረግ ወሳኝ ነው።
  • ለትርፍ ተብሎ ከሚሠራ አላስፈላጊ ውድድር ራስን ይጠብቃል፤ መሠረቱን ኢንተርኔት መር ማድረጉ በቀላሉ ማንም ሰው በፈለገው ጊዜ የሚጠቀምበት እንዲሆን ያስችለዋል።