“በብፅዕ አቡነ ሄኖክ ላይ እየተደረገ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻና ዛቻ አሳስቦናል” (የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት)

(አደባባይ ሚዲያ ሚያዝያ 16/2012 ዓ.ም፤ April 24/2020):- የምዕራብ አርሲ ሀ/ስብከት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሄኖክ ላይ እየተደረገ ነው ያለውን የስም ማጥፋት ዘመቻ አወገዘ።

ሀ/ስብከቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ብፁዕነታቸውን ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ፈልገው ያልተሳካላቸው ኃይሎች በፈጠራ ወሬ ያልተናገሩትን ተናገሩ በማለት በስፋት በማኅበራዊ ሚዲያ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደከፈቱባቸው ገልጿል።

በተጨማሪም ይህ ድርጊት በንቀትና በዝምታ ማለፍ ጉዳዩን እያባባሰው እንዳለ ጠቅሶ የሐሰተኞችን አካሄድ ማጋለጥ አስፈላጊ በመሆኑ መግለጫ ማውጣቱ አስፈላጊ መሆኑን አስታውቋል።

ሀገረ ስብከቱ እውነቱን ለምዕመናን ማሳወቁንና በተለይ የዋሃን ምዕመናን በሚናፈሰው የበሬ ወለደ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዳይረበሹና በሐተኛ አልሉባልታዎች ግራ እንዳይጋቡ አሳስቧል።

ሀ/ስብከቱ ብፁዕነታቸው በዘመነ ጵጵስናቸው ያስመዘገቡት አመርቂና አኩሪ ታላላቅ ሥራዎች እንዲሁም ታሪካዊ የብፁዕነታቸውን ተግባራት ገልፆ እነዚህን “የከሰሩ የፖለቲካ ነጋዴዎች ሴራ ማጋለጡንም” እንደሚቀጥል በመግለጫው አትቷል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል ከታች አያይዘን አቅርበነዋል።

Comments are closed.