ምርጫው ከፍልሰታ ጾም በኋላ እንዲሆን ተወሰነ

(አደባባይ ሚዲያ:-የካቲት 6/2012) መጪው ምርጫ ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚሆን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀጣዩን ሀገር አቀፍ ምርጫ በተመለከተ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በመከረበት ወቅት ነው ይህን የገለፀው።

ቦርዱ ከዚህ በፊት በጊዜያዊነት ነሐሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚከናወን አስታውቆት የነበረውን የምርጫ ቀን በርካታ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች በሱባኤ የሚያሳልፉበት ጊዜ በመሆኑ እንዲራዘም
ቀኑ እንዲለወጥ ሲጠየቅ መቆየቱ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት የምርጫ ቀኑን ወደ ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ማሸጋገሩን ቦርዱ አስታውቋል።

በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የምርጫ ክልል ካርታ ይፋ የሚሆነው መጋቢት 01/2012 ዓ.ም ይሆንና የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ደግሞ መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ይደረጋልተብሏል። የተፎካካሪ ፓርቲዎችና ግለሰቦች የመወዳደሪያ ምልክት ማቅረቢያና መወሰኛ ጊዜ ደግሞ ከሚያዝያ 16-30 ባሉት 15 ቀናት እንደሆነ ተገልጿል። የተረጋገጠ የምርጫ ውጤት ማሳወቂያ ጊዜም ከነሐሴ 24 እስከ ጳጉሜን 3/2012ዓ.ም እንደሚሆንም ነው ቦርዱ የገለጸው፡፡

አደባባይ ሚዲያ ቀደም ብሎ የወጣው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ቀን አግባብ እንዳልነበር ሲዘግብ መቆየቱ ይታወሳል::

Comments are closed.