አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ተገደለ

(አደባባይ ሚዲያ፤ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም)፡- ታዋቂው ኦሮምኛ ቋንቋ አቀንቃኝ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ዛሬ ማምሻውን ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን በቦታው የሚገኙ ምንጮች እየገለፁ ነው። በኦሮሞኛ የሙዚቃ ሥራዎቹ ታዋቂ የሆነው አርቲስት ሃጫሉ ዛሬ ማምሻውን “ገላን ኮንዶሚኒየም” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በግምት ከምሽቱ 3፡30 ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዜናው እጅግ አስደንጋጭ ሲሆን ይህንን ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች ለሕግ እንዲቀርቡ ጥሪአቸውን ያሰሙ የአደባባይ ቤተሰቦች ነገሩ ከእጅ ወጥቶ ወዳልተፈለገ ሌላ ቀውስ እንዳያመራ አሳስበዋል። ከዚህ በፊት አንድ አክቲቪስት «ተከብቤአለሁ» በማለቱ ምክንያት የብዙ ሰዎች ሕይወጥ መጥፋቱ ይታወሳል።

የአምቦው ልጅ፣ ልብ ቀስቃሹ አርቲስት ሐጫሉ የተነገረው ዜና ውሸት እንዲሆን ምኞታችን ነበር። ነፍስ ይማር። (ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ሙከራ እያደረግን ሲሆን እንዳገኘን ይዘን እንመለሳለን።)

Comments are closed.