በመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት እና በጃን ሜዳ ጉዳይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ማብራሪያ ጠየቀ

(አደባባይ ሚዲያ፤ ሚያዝያ 21/2012 ዓ.ም፤ April 29/2020)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመስቀል አደባባይ ላይ የሚሰራውን ግልጽነት የጎደለው ፕሮጀክት ምንነት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ጠየቀ።

መንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤቱ እንዳለው ቤተ ክርስቲያን በዓለ መስቀልን የምታከብርበት እንዲሁም የቦታው ጥንታዊ ባለቤት እንደ መሆንዋ የሚሠራው ሥራ ሊነገራትና ልታውቀው ይገባል በማለት ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤቱን በደብዳቤ ጠይቋል።

በተጨማሪም በዓለ ጥምቀት የምታከብርበት ጃን ሜዳ ለገበያ ማእከልነት እንዲውል መደረጉ ተገቢ ባለመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ማብራሪያ እንዲሰጠው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በተጨማሪ ጠይቋል።

Comments are closed.