ጠቅላይ ቤተ ክህነት በከፊል ተዘጋ መንፈሳዊ ኮሌጆችና የአብነት ት/ቤቶች ሙሉ ለሙሉ እዲዘጉ ተወስኖአል።

(አደባባይ ሚዲያ መጋቢት 16/2012ዓ,ም Adebabay Media March 26/2020 )

አለም አቀፍ ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ይረዳ ዘንድ ቤተ ክርስቲያኒቱ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ ቀጥላለች ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዛሬ በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በብፁዕ አቡነ ያሬድ አማካኝነት በሰጠው መግለጫ በጊዜያዊነት የሚዘጉ የሥራ ክፍሎችንና ተቋማትን አሳውቋል ።

1,ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምረው በሙሉ የተዘጉት
ሀ, የመንበረ ፓትርያርክ ቅርሳቅርስ ቤተ መጽሐፍት ወመዘክር
✔ጉብኝት
✔የንባብ አገልግሎት

2,በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሥር ያሉ
ሀ,መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲዎች
ለ,መንፈሳዊ ኮሌጆች
ሐ,የካህናት ማሰልጠኛ
መ,መዋዕለ ሕፃናት
ረ,የአብነት ትምህርት ቤቶች ተዘግተው የመማር ማድተማሩ ሂደት ተቋርጦ ተማሪዎች እቤታቸው ተቀምጠው እንጠኑ እንዲቆዩ።

3,በከፊል እንዲዘጉ የተደረጉ

ከመንበረ ፓትርያሪክ ጀምሮ እስከ አህጉረ ስብከቶች አስፈላጊና አስቸኳይ ስራ ብቻ ሲፈለጉ እየተመላለሱ ከሚሰሩት ውጭ ሌሎች እቤታቸው እዲቀመጡ ሲሉ ጠቅላይ ሥራአስኪያጁ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል ።

Comments are closed.