አቡነ ሩፋኤል ምን ገጠማቸው? ታገቱ? ተዘረፉ? ወይስ የጠላት ወሬ ነው?

(አዲስ አበባ መጋቢት 9/2012 ዓ.ም፤ March 18/2020) የጋምቤላና የምዕራብ ወለጋ እንዲሁም የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ማንነታቸው «ለጊዜው ባልታወቁ ኃይሎች የመታፈናቸውን ጉዳይ» የአደባባይ ምንጮች እንዳደረሱን ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ቤተ ክህነት እና ወደ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መደወል ያዝን። ካገኘናቸው አባቶች መካከል አንዱ «አዎ ብፁዕነታቸው ላለፉት 10 ቀናት ድምጻቸው አልተሰማም። ስለ ጉዳዩ ከአካባቢው ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ሪፖርት ተደርጓል፤ እኛም እየተከታተልን ነው» የሚል ምላሽ ሰጡን። ቀጥሎ ያደረግነው ሌሎች ምንጮችን ለማጣራት መሞከር ነበር። እነርሱም ተመሳሳይ መረጃ እንዳላቸው አረጋገጥን። የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤትም ጉዳዩን በተመለከተ ለመንግሥት ሪፖርት እንዳደረገ ማረጋገጥ ችለናል። ለዚያም ነው የዘገብነው።

ቀጥሎ የሚመጣው ጥያቄ ብፁዕነታቸው 10 ቀን የት እንደነበሩ ማረጋገጥ እና በአካባቢው የስልክ ግንኙነት ካለመኖሩ ባሻገር ለምን ድምጻቸውን እንዳጠፉ ማጣራት ነው። ሥራችን የሆነውን ሆነ ያልሆነውን አልሆነም ብሎ መዘገብ ነው። እንዲሁም የቀረበው ዘገባ ከቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጀምሮ ያለውን መረጃ ያካተተ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።
ለማንኛውም ይህንን ቃለ ምልልስ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።

Comments are closed.