የ “OMN” ሚዲያ የኢትዮጵይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ይቅርታ እንዲጠይቅ ታዘዘ::

የብሮድካስት ባለስልጣን ማስጠንቀቂያ ለሚዲያው ማስጠንቀቂያ ላከ::

( አደባባይ ሚዲያ:- የካቲት 18/2012) የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በጃዋር አህመድ ባለቤትነት የሚሰራጨውን “የ ኦ ኤም ኤን” (Omn) ሚዲያን አስጠነቀቀ::

ሚዲያው በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ባስተላለፈው የሀሰት ትርክት እና መሰረተቢስ ፕሮፖጋንዳ እንዲሁም የስም ማጥፋት ዘገባ የተነሳ ነው ማስጠንቀቂያው የደረሰው:: ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው በኦፌኮ ፓርቲ ቅስቀሳ መድረክ ላይ የቤተ ክርስቲያኗን ስም ያላግባብ እያነሳ የተሳሳተ ውንጀላ ሲያደርግ የነበረውን የአቶ ኀይለሚካኤል ንግግር በቀጥታ ስርጭት በማስተላለፉ በአዋጅ የተከለከለን ህግ ተላልፏል ሲል ነው ማስጠንቀቂያውን የላከለት::

በቤተክርስቲያኗ ላይ የተላለፈውን ውንጀላ ጠቅሶ ቅሬታ ያቀረበው የጴጥሮሳዊያን ማኅበር እንደሆነም ባለስልጣኑ ገልፅጿል::

ሚዲያው የውንጀላ ንግግሩን ባስተላለፈበት ተመሳሳይ ስዓት እና የፕሮግራም ይዘትም ስህተቱን እንዲያርም እና ቤተክርስቲያኗን ይቅርታ እንዲጠይቅም ታዟል::

Comments are closed.