በኤምሬትስ የቤተ ክርስቲያን ይዞታ ጥያቄ መልስ አገኘ

(አደባባይ ሚዲያ :- የካቲት 5 /2012 ዓ.ም፤ Frb. 13/2020):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ለበርካታ ጊዜ ሲነሳ የነበረው ለቤተ ክርስቲያን መስሪያ የሚውል የግንባታ ቦታ ጥያቄዋ መልስ ማግኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለፁት ዛሬ ምሽት በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ተወካዮች ጋር በአቡዳቢ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።
ቀደም ብለው ጉዳዩን በትኩረት ሲከታተሉት የነበሩት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሊቀ ጳጳስ ብፁእ አቡነ ዲሜጥሮስ እግዚአብሔር በጊዜው ስላደረገልን ደስ ብሎናል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል:: @ማኅቶት ቲዩብ

Comments are closed.